አልኮልን አዘውትሮ መጠጣት በአንጎል ዋነኛ ክፍል የሚፈጠሩ ህዋሶችን እንደሚገድል ጥናት አመለከተ

ህዳር 04፣2010

አልኮልን አዘውትሮ መጠጣት በአንጎል ዋነኛ ክፍል የሚፈጠሩ ህዋሶችን እንደሚገድል ተመራማሪዎች አመለከቱ፡፡

በአሜሪካ የቴክሳስ ህክምና ቅርንጫፍ ተመራማሪዎች ባደረጉት ጥናት አልኮልን አዘውትሮ መጠጣት በአንጎል ዋነኛ ክፍል ላይ የሚፈጠሩና ለነርቭ ህውሶች መፈጠር ምክንያት የሚሆኑ አዳዲስ ህዋሶችን እንደሚገድል ገልፀዋል፡፡

በተለይም ሴቶች በጉዳቱ ግንባር ቀደም ተጠቂዎች እንደሚሆኑ ተመራማሪዎቹ በአይጦች ላይ ባደረጉት ጥናት የምርምር ግኝታቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ጥናቱ በአልኮል ጫና ምክንያት በሴቶችና በወንዶች መካከል የአዕምሮ ለውጥ የተለያየ መሆኑን ለመጀመሪያ ግዜ ያሳየ ጥናት ሆኗል፡፡

አልኮልን አዘውትሮ መውሰድ ጫናው በአንጎል ላይ የሚያሳድረው ጫና ከፍተኛ በመሆኑ ጥንቃቄ የሚያሻ መሆኑን የጥናታቸው ውጤት እንደሚያሳይ ተመራማሪዎቹ ተናግርዋል፡፡

ግኝቱ  ከባድ የሆነን የአልኮል ሱሰኝነት በርን ለመዝጋት መነሻ ሆኖ እንደሚያገለግልም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፡‑ ሽንዋ