የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2ዐ ሰዎች የዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ህክምና አደረገ

ህዳር 3፣2010

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 2ዐ ሰዎች ሙሉ በሙሉ የዳሌ መገጣጠሚያ  ቅየራ ህክምና ተደረገላቸው፡፡

ዜጐቹ ህክምናውን በውጭ ሀገር ቢያከናውኑ ኖሮ ከ3 እስከ 5 መቶ ሺ ብር ወጪ ያስወጣቸው እንደነበር ተገልጿል፡፡

ህክምናውን በሀገር ውስጥ በበቂ ደረጃ ለመስጠት አጥንት ውስጥ የሚገባው ሰው ሰራሽ መገጣጠሚያ መሆኑ የዘርፉ ፈተና ነው፡፡

ሪፖርተራችን አዲስህይወት ተስፋዬ ተከታዩ ዘገባ አዘጋጅታለች፡፡