ህብረተሰቡ ከስኳር ህመም ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ

ሕዳር 3፣2010

ህብረተሰቡ የአኗኗር ዘይቤውን በማስተካከል ከስኳር ህመም ራሱን እንዲጠብቅ የኢትዮጵያ የስኳር ህሙማን ማህበር ጥሪ አቀረበ፡፡

ማህበሩ 26ኛውን የአለም የስኳር ቀን ሴቶችና ስኳር በሚል መሪ ቃል በእግር ጉዞና በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል፡፡

የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶክተር አብዱራዛቅ  አህመድ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የስኳር ህሙማን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል ብለዋል፡፡

ከዚህ አኳያ ህብረተሰቡ የአኗኗር ዘይቤውን በማሻሻል ስኳርን ጨምሮ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ 6 ሚሊየን ሰዎች ከስኳር ህመም ጋር ይኖራሉ ተብሏል ሲል ሪፖርተራችን አማረ ተመስገን ዘግቧል፡፡