ኤርትራ ኢትዮጵያንና ጂቡቲን የሚቃወሙ ታጣቂ ቡድኖችን ትረዳለች ሲል ተመድ ከሰሰ

ህዳር 02፤2010

ኤርትራ ኢትዮጵያንና ጂቡቲን የሚቃወሙ ታጣቂ ቡድኖችን ድጋፍ መስጠቷን አሁንም እንደቀጠለችበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል፡፡

ይህ የኤርትራ ዋንኛ ዓላማም በሁለቱ ሃገራት ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር ያደረገ ነው ብሏል፡፡

የጉዳዩ ሪፖርት ለጸጥታው ምክር ቤት በቀረበበት ወቅት እንደተገለጸው ኤርትራ ድጋፏን ለታጣቂ ቡድኖች ድጋፍ መስጠት ብትቀጥልም በሁለቱ ሃገራት ላይ ምንም አይነት ስጋት አልፈጠረም፡፡

በሪፖርቱ መሰረት የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻ አውጪ ንቅናቄ፤ የአንድነትና ዲሞክራሲ ግንባታ ግንባር፤ የግንቦት ሰባት እና የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አሁንም ከኤርትራ ድጋፍ የሚያገኙ ታጣቂ ቡድኖች ናቸው፡፡

ምንጭ፡ አፍሪካ ኒውስ