በአሜሪካ የአየር ላይ ጥቃት በርካታ የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ

ሕዳር 01፣2010

አሜሪካ ጥቅምት 30/2010 ዓ.ም በሶማሊያ በሰው አልባ አውሮፕላን በወሰደችው የአየር ጥቃት በርካታ የአልሸባብ ታጣቂዎች መግደሏን አስታወቀች፡፡

ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ምዕራባዊ ክፍል 160 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ባይ በተባለች የአገሪቱ ግዛት በተካሄደው የአየር ድብደባ ንጹሀን ዜጎች እንዳልጎዳ በአፍሪካ የአሜሪካ ዕዝ ገልጿል።

በሶማሊያ በሽብር ቡድኑ ላይ እየተፈጸሙ  ያሉ የአውሮፕላን ድብደባዎች ከሶማሊያ መንግስት ጋር በመተባበር እየተካሄዱ መሆናቸውንም አሜሪካ አመልክታለች።

አሜሪካ በተያዘው የአውሮፓውያኑ አመት በሶማሊያ በሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎች ላይ 22 ጊዜ የአየር ድብደባ ማካሄዷን ዘገባው አመልክቷል።

ምንጭ- አይስላንድ ፓኬት