ኡጋንዳ አምስት ሺህ ወታደሮችን ወደ ሶማሊያ ለመላክ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

ጥቅምት 30 ፤2010

ኡጋንዳ ከአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ተልዕኮ ውጪ አልሻባብን ለመደምሰስ አምስት ሺህ ወታደሮችን ወደ ሶማሊያ ለመላክ ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች፡፡

አለም አቀፉ ህብረተሰብ የሚያስፈልገውን ወጪ የሚሸፍንላት ከሆነ ኡጋንዳ ወታደሮቿን ለመላክ ፍቃደኛ መሆኗን ገሪቱ ጦር ቃል አቃባይ ብርጋዴር ሪቻርድ ካሬሚሬ ገልጸዋል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዩቬሪ ሞሴቬኒም ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ጋር መምከራቸው ተገልጿል፡፡

ሀገሪቱ ከምትፈልጋቸው እርዳታዎች መካከል የገንዘብ፤ የጦር መሳሪያዎች በተለይም ሄሊኮፕተሮችና የመሳሰሉት እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡ ሺንዋ