ሞሮኮ የመጀመሪያውን ሳተላይት አመጠቀች

ጥቅምት 29፣2010

ሞሮኮ ለወታራዊ እንቅስቃሴዎችና ለድንበር ደህንነት ቁጥጥር የሚውል የመጀመሪያውን ሳተላይት አመጠቀች፡፡

ሳተላይቱ የሀገሪቱን በረሀማ አካባቢዎችን የተፈጥሮ አደጋዎች በቀላሉ ለመቆጣጠር ያግዛል፡፡

አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ወጪ እስከአሁን ይፋ አልተደረገም፡፡

2ተኛውን ሳተላይት እ.ኤ.አ በ2ዐ18 ለማምጠቅ እቅድ ተይዟል፡፡

የአሁኑ የሞሮኮ ሳተላይት ማምጠቅን ተከትሎ የጎረቤት ሀገር አልጄሪያና የስፔንን ትኩረት ስቧል፡፡