ትዊተር የመፃፊያ ፊደሎቹን ብዛት መጠን በእጥፍ ሊያሳድግ ነው

ጥቅምት 29፣2010

ትዊተር የመፃፍያ ፊደሎቹን ብዛት መጠን ወደ 280 ሊያሳድግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ትዊተር ለብዙሃን ተጠቃዎቹ እንዲሆን አሁን ካለው የመፃፊያ ባህሪ ማለትም የፊደላት ብዛት መጣኔን ከነበረበት 140 ወደ 280 ለማሳደግ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

አዲሱ የትዊተር የመፃፊያ ፊደላት ወሰን ቁጥር ላይ መሻሻያ መደረጉ

ለጃፓን፣ ለቻይናና ኮሪያ ትዊተር ተጠቃሚዎች በአንድ ፊደል መፃፊያ ብዛት ያለው መልዕክት ማስተላለፍ ስለሚያስችል  ማሻሻያው አይመለከታቸውም ተብሏል፡፡

ትዊተር ማሻሻያ ለማድረግ የወሰነው የመፃፊያ ምጣኔው ውስን ሆኖ ተጠቃዎቹ ትችት በማቅረባቸው ነው ተብሏል፡፡

የፊደል መፃፊያ ምጣኔው መጨመሩ የተጠቃሚዎቹን ተሳትፎ የበለጠ እንደሚያሳድግለት  ትውተር አስታውቋል፡፡   

ምንጭ፡‑ ቢቢሲና ዋሽንግተን ፖስት