አወዛጋቢው የዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በቀጣይ ዓመት ይካሄዳል

ጥቅምት 27፣2010

አወዛጋቢው የዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በቀጣይ ዓመት   እንዲካሄድ ቀን ተቆረጠለት፡፡

የአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ትላንት ይፋ እንዳደረገው ባለፈው ዓመት መካሄድ የነበረበትና በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ የስልጣን ጊዚያቸው ማብቂያ  ሊበጅለት ይገባል የሚል ተቃውሞ በመነሳቱ እስካሁን መቋጫ ሳያገኝ ቆይቶ ነበር፡፡ ይሁንጂ እንደ ምርጫ ኮሚሽኑ  ከሆነ  እ.ኤ.አ በቀጣዩ ዓመት ታህሳስ መጨረሻ 2018 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ቀን ተቆርጦለታል፡፡

43 ሚሊዮን የሚሆኑ የዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ዜጎች ድምጻቸውን ለመስጠት ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ ይግኛሉ፡፡

የምርጫው ውጤትም  በሁለት ሳምንት ጊዜ  ውስጥ እንደሚገለጽ ከወዲሁ ተወስኗል፡፡

የአገሪቱ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በ2016 ይካሄዳል ቢባልም በተደጋጋሚ ሲሰረዝ እንደነበር የሚታወስ ነው᎓᎓

እ.ኤ.አ 2001 አባታቸውን ተክትው ወደ ስልጣን የመጡት ጆሴፍ ካቢላ የስልጣናቸው ጊዜ ያቃ የሚል ህዝባዊ ተቃውሞ ቢገጥማቸውም በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ላይ ይሳተፉ አይሳተፉ ግን የተገለፀ ነገር የለም፡፡

ምንጭ፡‑ ሲጂቲኤን