የኢትዮጵያ የጂኦተርማል እምቅ ሃብቷ በሳተላይት ምስል ማወቅ ተችሏል

ጥቅምት 26፤2010

ኢትዮጵያ ያላትን የጂኦተርማል እምቅ ሃብትን ለማወቅ በሳተላይት ምስል የታገዘ ጥናት የኢትዮጵያ እንግሊዝ ተመራማሪዎች መለየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከሁለቱ ሃገራት የተውጣጡት የተመራማሪዎች ቡድን እንዳስታወቀው ከሆነ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የጂኦተርማል እምቅ ሃይል አላት፡፡

በጥናቱ መሰረትም ሀገሪቱ እስከ 10 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት የሚችል የጂኦተርማ እምቅ ሃብት እንዳላት ተገምቷል፡፡

ከአሉቶ ላንጋኖ የጂኦተርማል ሃይል ማመንጫ 70 ሜጋ ዋት ለማልማት የግንባታ ስራው እየተከናወነ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በሳተላይት የታገዘ ጥናት መደረጉ ጊዜንና ሃብትን ከመቆጠቡም ባሻገር ሰፊ ቦታን የሚያካልል ጥናትን በቀላሉ ማድረግ እንደሚያስችል ቡድኑ ገልጿል፡፡

ይህ የተገኘው የጥናት ውጤትም በሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ሃገራት ተመሳሳይ ምርምር ለማድረግ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡ ቲንክጂኦኢነርጂ