አፍሪካ በግብርና ዘርፍ ለአረንዴ አብዮት ማዕከል ለመሆን እየተጋች መሆኑ ተገለፀ

ጥቅምት 24፣2010

በአፍሪካ ባለፈው አስር ዓመት በግብርና ዘርፍ የታየው እድገት አህጉሪቱ የአረንዴ አብዮት ማዕከል እንድትሆን እያደረጋት ነው ተባለ፡፡

እ.ኤ.አ በ2030 የአፍሪካ የግርብና ዘርፍ 1 ትሪሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ምርት ሊያስመዘግብ እንደሚችል የአለም ባንክ መረጃ ያመለክታል፡፡

በአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለፀጋ የሆኑት ናይጄሪያዊ ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ ደግሞ አፍሪካ በግብርና ዘርፍ በምታስመዘግበው ምርት የአለም የምግብ ቅርጫት ትሆናለች ብለዋል ኒዎርክ ላይ የተባበሩት መንግስታ ባዘጋጀው መድረክ ፡፡

ሆኖም በዘርፉ ያለው የቴክኖሎጂና የኢንቨስትመንት እጥረቶች እንዲሁም በዘርፉ የሚሰማራ ወጣት የሰው ሀይል አናሳ መሆን በግብርውና ሴክተር ይህን የአህጉሪቱን ራዕይ ለማሳካት ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ችግሮች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

ባለፈው አስር ዓመት ብቻ የአፍሪካ የግብርና ዘርፍ ቀጣይነት ያለው እድገት ቢመዘገብበትም በቀጣይ ብዙ ሊሰራ ይገባ ነው የሚባለው፡፡

በግብርውና ዘርፍ በአውሮፓ፣ ሰሜና አሜሪካና ኢሲያ ያለው ታሪካዊ ተሞክሮ እንደሚያሳየው ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት ሊመዘገብ የሚችለው በአንስተኛ ማሳ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ እንደሆነ ይነገራል፡፡

በዚህ መሰረት በአፍሪካ በግብርና መስክ ከተሰማራው ውስጥ 80 በመቶው የሚሆነው በአንስተኛ ማሳ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ናቸው፡፡

በዘርፉ ሰፋፊ የግብርና እርሻዎችን ከማልማት ይልቅ የአርሶ አደሮችን አነስተኛ ማሳ ምርታማነት መጨመርና የግብርና ምርቶች እሴት እንዲጨመርባቸው የአምራች ኢንዲስትሪዎችን አቅም ማጎልበት የተሻለ ውጤት እንደሚያመጣ የብዙዎች እምነት ነው ተብሏል፡፡

እ.ኤ.አ በ2003 የአፍሪካ ግብርና ዘርፍን ለማሳደግ የአህጉሪቱ ሀገራት አጠቃላይ የአፍሪካ የግብርና ልማት መርሃ-ግብርን አጽድቀው ነበር፡፡

ይህም መርሃ ግብር የአህጉሪቱ መንግስትታ ከብሔራዊ በጀታቸው 10 በመቶ የሚሆነውን ለዘርፉ እንዲመድቡ ይጠይቃል፡፡

ኢትዮጵያና ናይጄሪያ ደግሞ ለግብርና መስክ ትኩረት በመስጠት ስማቸው ከሚነሳ የአፍሪካ ሀገሮች ተርታ እንደተሰለፉ ተነግሯል፡፡

እ.ኤ.አ በ2017 የአፍሪካ የአረንጓዴ አብዮት ፎረም በአቢጃን ኮትዲቯር በተካሄደበት ወቅት  በግብርናው ዘርፍ የመንግስት ድክመት በሚታይበት መስኮች ያለውን ችግር ለመቅረፍ በዘርፉ የግል ኢንቨስትመንት ተሳትፎ ማጠናከርና የቴክኖሎጂ እውቀት ሽግግር እንዲኖር በማድረግ አንስተኛ ማሳ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማደረግ ይቻላል ነው የተባለው፡፡

28 የአፍሪካ ሀገሮችን የሰብል ምርቶች ላይ ጉዳት እያስከተለ ያለው የአሜሪካ መጤ ተምች ድግሞ ለግብርናው ምርት ከፍተኛ ስጋት በመሆኑ አፋጣኝ እልባት ሊበጅለት ይገባል ተብሏል፡፡

አነስተኛ ማሳ አርሶ አደሮች ለግብርና ስራቸው ማንቀሳቀሻ የሚውል ገንዘብ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚገባም ተመልክቷል፡፡

በግብርናው ዘርፍ በአለም ገበያ የተሻለ ገቢ ለማግኘት የአፍሪካ ሀገሮች ምርቶችን በጥሬው ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምረው ቢልኩ የተሻለ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸውም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ ሄራልድ