ኩባንያው ሲጋራ ለማያጨሱ ሰራተኞቹ ተጨማሪ የስድስት ቀናት ዕረፍት ሰጠ

ጥቅምት 23፣2010

አንድ የጃፓን ኩባንያ ሲጋራ ለማያጨሱ ሰራተኞቹ በአመት ተጨማሪ የስድስት ቀናት ዕረፍት ሰጠ።

በጃፓኗ ርእሰ ከተማ ቶክዮ መሰረቱ ያደረገው ፒላ ኩባንያ ሲጋራ ለማያጨሱ ሰራተኞቹ በአመት ከሚሰጣቸው ተጨማሪ የስድስት ቀናት እረፍት መስጠት ጀምሯል።

ሲጋራ አጫሽ ሰራተኞች ከማያጨሱ ሰራተኞች አንጻር ያነሰ ስራ መስራታቸው ለውሳኔው ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

የኩባንያው ቃል አቀባይ ሂሮታካ ማሱሺማ ሲጋራ አጫሾችን አንቀጣም ባለማጨሳቸው ግን እናበረታታቸዋለን ብለዋል።

ሲጋራ አጫሽ ሰራተኞች አንድን ሲጋራ ለማጨስ አስራ አምስት ደቂቃ እንደሚያጠፉ ቃል አቃባዩ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት አጫሽ ሰራተኞች በየቀኑ 40 ደቂቃ ከስራቸው እንደሚነሱ ኩባንያው ገልጿል።

በጃፓን ከአምስት ሰዎች አንዱ አጫሽ መሆኑ ዘገባው አመልክቷል።

ምንጭ፤ ኤ.ቢ.ሲ