የአለም ሙቀት መጨመር በህዝቦች ጤንነት ላይ ጉዳትን ጋርጧል ፡‑ ተመራማሪዎች

ጥቅምት 21፣2010

የአለም ሙቀት መጨመር የህዝብ ጤንነትን እየጎዳ መሆኑን የሀኪሞችና ተመራማሪዎች ቡድን አስታወቀ።

ይሁን እንጂ ምድራችን የድንጋይ ከሰል መጠቀሟን ከቀነሰች  ለችግሩ መሻሻል  ተስፋ እንዳላት አመልክተዋል።

ድሆችና በእድሚያው የገፉ ሰዎች ጤና እየተባባሰ በመጣው የአየር ንብረት ለውጥ ስጋት ውስጥ መውደቁን ግኝቱ አመልክቷል፡፡ይሁንእንጂ እ.ኤ.አ ከ2015ቱ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት በኋላ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን የካርቦን ልቀት  ለመቀነስ ከስምምነት መደረሱ ለሰው ልጆች ጤና ተስፋ ሰጨ ዋስትና ሆኖ መታየቱን ተመራማሪቹ ገልፀዋል፡፡

ጥናቱ እንደሚያመለክተው የጤና ጠንቆች  የሚመነጩት ዘውታሪ ከሆኑ የሙቀት ሞገዶች በመሆኑ በሽታዎች በነፍሳት፣ በአየር ብክለትና በሌሎች መንገዶች መተላለፈፋቸው አይቀሬ ነው፡፡ይሁን እንጂ የሰው ልጅ የጤና መጠበቂያ መድህኑን በየጊዜው እያሻሻለ በመምጣቱ በምድራችን ላይ የሚመዘገበው ሞት ያን ያህል አስደንጋጭ አይደለም ተብሏል፡፡ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ያጤኑ ተጨማሪ ምርምሮች እንደሚያስፈልግ ግን  ጥናቱ አመልክቷል፡፡

ከአውሮፓውያኑ 1990 ጀምሮ በየአስር አመቱ የ58.4 ሚሊዮን ታማሚዎች ቁጥር  በእጥፍ እየጨመረ መጥቶ  በ2013 10 ሺህ ሰዎች ያህል ለሞት ተዳርገዋል።

በአውሮፓውያኑ ከ2000 እስካለፈው አመት ዕድሚያቸው ከ65 አመት በላይ የሆኑ ለሙቀት አምጭ በሽታዎች የተጋለጡ ሰዎች 125 ሚሊዮን መጨመሩ ተገልጿል።

የአየር ንብረት ለውጡ ከምግብ እጥረት ጋር በመያያዙ በጤና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳረፉ አይቀርም ብሏል ጥናቱ፡፡

ተመራማሪዎች ከሰው ልጅ ጤና ምርመራ ጋር በማነጻጸር ባወጡት ሪፖርት እንዳመለከቱት ምድራችን ጥበቃ ያስፈልጋታል።

የአየርን ብረት ለውጥ አደጋ ምልክቶች እየታዩ ቢሆኑም ተስፋ ሰጪ ሁነቶች እንዳሉም ተመልክቷል።

ከመላው ዓለም የተውጣጡ 63 የህክምና ጠበብቶች፣የህብረተሰብ ጤና ባሙያዎች፣እና የአየር ንብረት ለውጥ ተመራማሪች በጥናቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ምንጭ፡‑ ኢቢሲ ኒውስ