አንዳንድ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ህዝብን ከህዝብ ጋር በሚያጋጭ መልኩ የሚያቀርቡት ዘገባ ተገቢ አለመሆኑን መንግሥት ገለፀ

ጥቅምት 13፣2010

በኦሮሚያ የተወሰኑ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶችን በተመለከተ አንዳንድ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን አንድን ብሔር ከሌላ ብሔር ጋር በሚያጋጭ መልኩ የሚያቀርቡት ዘገባ ተገቢ አለመሆኑን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትር ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ገለፁ፡፡

የሚዲያ ነፃነትን ሕዝብን ለሚጎዳ ተግባር ማዋል ተገቢ አለመሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ሪፖርተራችን ብሩክ ያሬድ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡