የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

ጥቅምት 13፣2010

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ አልሻባብን በጋራ መመከት የሚያስችል ድጋፍ ለመጠየቅ ዛሬ ረፋድ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዝዳንቱ አልሻባብን በጋራ መመከት የሚያስችል ድጋፍ ለመጠየቅ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ ሰሞኑን በሞቃዲሾ በደረሰው ከፍተኛ የሽብር ጥቃት ኢትዮጵጵያ ላደረገችው ድጋፍም አመስግነዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ከጠቅላይ ሚንስትር ያምደሳለኝ ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።