ጃፓናዊያን ፕሬዝዳንት አቤ በጠሩት ድንገተኛ ምርጫ ተወካዮቻቸውን እየመረጡ ነው

ጥቅምት 12፣2010

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ባለፈው ወር በጠሩት ድንገተኛ ምርጫ መሰረት በሀገሪቱ ዛሬ ምርጫ እየተካሄደ ነው፡፡

ፕሬዝዳንት አቤ ከሰሜን ኮሪያ እየተቃጣባት ያለውን ስጋትና ሌች አገራዊ ቀውሶችን ተከትሎ  ነው የታችኛው ምክር ቤታቸውን በትነው ድንገተኛ ምርጫ እንዲካሄድ የጠሩት፡፡

ፕሬዝዳንት አቤ በምርጫው አብላጫ ድምፅ በማግኘት የመንግስታቸውን የመወሰን አቅም ከፍ ለማድረግ  ይጠቀሙበታል ተብሏል፡፡

ሺንዞ አቤ ምርጫውን የሚያሸንፉ ከሆነ ሊተገብሯቸው ያሰቧቸውን አዳዲስ ፖሊሲዎች በአዲስ መንፈስ ለመስራት የሚያስችላቸው ይሆናል፡፡

ፕሬዝዳንት አቤ ምርጫውን እንዳሰቡት በአብላጫ የሚያሸንፉ ከሆነ በሰሜን ኮሪያ ስጋት ዙሪያ፣በድህረ ፉኩሽማ የኒውክለር ጫና ዙሪያና አወዛገቢ በሆነው የታክስ ማሻሻያ ዙሪያ አዳዲስ ፖሊሲዎችን የሚተገብሩ ይሆናል፡፡

ፕሬዝዳንት አቤ በጠሩት ድንገተኛ ምርጫ በአብላጫ ድምፅ የማሸነፍ እድል እንዳላቸው ቀደም ብሎ በወጣ ተተንብዮላቸዋል፡፡

ተቀዋሚዎቻቸውም ቢሆን የተዳከሙበት ወቀት ከመሆኑ አንፃር አጋጣሚውን ፖለቲካዊ  ትርፍ ሊያገኙበት ይችላል ተብሏል፡፡

ጃፓናዊያን ታይፉን የተሰኘው ወጀብ አዘል ውሽንፍር ሳይበግራቸው  ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ላይ መሆናቸውን የቢቢሲ መረጃ ያመለክታል፡፡