የኃይማኖት አባቶች ግጭቶች እንዳይፈጠሩ እንዲሰሩ የኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ

ጥቅምት 11፣2010

በቅርቡ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረው ግጭት የሀገሪቱን አብሮ የመኖር ታሪክ የማይወክል በመሆኑ የኃይማኖት አባቶች ተመሳሳይ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ እንዲሰሩ የኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡

ምክር ቤቱ በአዋሳኝ አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት ዙሪያ የሰላም ኮንፈረንስ አካሂዷል፡፡