የኢራቅ ጦር የኪርኩክ ግዛት መቆጣጠሩን አስታወቀ

ጥቅምት 11፣2010

የኢራቅ ጦር የኪርኩክ ግዛትን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠሩን አስታወቀ፡፡

ጦሩ ግዛቲቱን የተቆጣጠረው ከኩርድ ሀይሎች ጋር ለሰዓታት የዘለቀ ከፍተኛ ፍልሚያ ካካሄደ በኋላ ነው፡፡

የኩርድ ሀይሎች ግን ኪርኩክ ከእጃቸው ስለመውጣቷ የሰጡት ማረጋገጫ የለም፡፡ የኢራቅ ጦር በአርቢስ አቅራቢያ የምትገኘው የአልተን ኩኘሪ ከተማንም መቆጣጠሩ ገልጿል፡፡

የኢራቁ ጠቅላይ ሚንስትር ሀይደር አል አባዲ በግጭቱ ሳቢያ ንፁሀን ዜጐች እንዳይጐዱ በማሰብ ጦራቸው ወደ አሪቢስ ከተማ ዘልቆ እንዳይገባ አግደዋል፡፡

የኩርድ ፔሸመርጋ ሀይል በነዳጅ ሃብቷ በኢራቅ 2ኛ የሆነችውን የኪርኩክን ግዛት የተቆጣጠሩት እ.አ.አ በ2ዐ14 አጋማሽ ነበር።

ኪርኩክ የማዕከላዊ ኢራቅ መንግስትና የኩርድ አስተዳደር የይገባኛል ጥያቄ መነሻ ሆኗ መቆየቷን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡