ዴኢህዴን በክልሉ መቻቻልና አንድነት እንዲሰርጽ ማድረጉን አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ገለፁ

ጥቅምት 10፤2010

በደቡብ ክልል የሚገኙ በርካታ ብሄረሰቦች በመቻቻልና በአንድነት እንዲኖሩ የደኢህዴን ህዝባዊ የመሪነት ባህሪ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ገለፁ፡፡

አቶ ሽፈራው ይህን ያሉት የደኢህዴንን አመሰራረትና የትግል ጉዞ የሚዳስስ የፓናል ውይይት በተካሄደት ወቅት ነው፡፡