ሰዎች ከሞቱ በሃላ አዕምሮአቸው ለተወሰነ ጊዜ ንቁ እንደሚሆን አንድ ጥናት ይፋ አደረገ

ጥቅምት 10፤2010

ሰዎች ህይወታቸው ካለፈ በኋላ ጭንቅላታቸው ለተወሰነ ጊዜ ስለሚሰራ ከህልፈ ህይወታቸው በኋላ መሞታቸውን እንደሚያቁ አንድ ጥናት አመልክቷል፡፡

በአሜሪካ ኒውዮርክ የሚገኙ የጥናቱ ባለቤቶች ይህን አዲስ ግኝት የደረሱበት በልብ በሽታ የተጠቁ ታማሚዎች ላይ ባደረጉት ምርምር ነው ተብሏል፡፡

ከተመራማሪዎቹ መካከል ዶ/ር ሳም ፓርኒያ እንዳሉት የሰዎች ህይወት የሚያልፈው የልብ ምታቸው ሲቆም ነው ፡፡

ይሁን እንጂ ሰው ሲሞትና ከጭንቅላት በታች ያሉ የሰውነት ክፍሎች መስራት ሲያቆሙ አዕምሮ ግን ለተወሰነ ጊዜ ንቁ ሆኖ ስለሚቆይ የሞተው ሰው በአካባቢው የሚደረጉ ድርጊቶችን ያያሉ፣ ይሰማሉ ተብሏል፡፡

ሰዎች ከሞቱ በኋላ አዕምሮ ስራውን ከማቆሙ በፊት በውስጡ ምን እንደሚፈጠር ለማወቅ ተመራማሪዎቹ ተጨማሪ ጥናት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ዊይቭብ፤ ሳይንስ ላይቭ