የፈረንሳዩ ኢንጂ ኩባንያ ከጸሃይ ሃይል ኤሌክትሪክ ሃይልን በአፍሪካ ተደራሽ ለማድረግ አቅዷል

ጥቅምት 10፤2010

የፈረንሳዩ የጋዝ ኩባንያ ኢንጂ የዩጋንዳን የጸሃይ ሃይል ማመንጫ ኩባንያን በመግዛት አገልግሎቱን ከሰሃራ በታች ለሚገኙ አገራት በማዳረስ የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎትን ለማዳረስ ማቀዱን ገልጿል፡፡

 ኩባንያው እንደገለጸው የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ቁሶችን የሚያመርተውን  ፌኒክስ ኢንተርናሽናልን በመግዛት ነው ወደ አፍሪካ ገበያ የገባው፡፡

ለሚያቀርበው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትም አነስተኛ ዋጋ የሚጠይቅ ሲሆን ክፍያውም በደንበኞቹ ሞባይል አገልግሎት በኩል የሚፈጸም ነው፡፡

ኢንጂ ኩባንያ ሶስት ሺህ ሜጋ ዋት ሃይል ከታዳሽ ሃይልና ከጋዝ ለማምረት የሚያስችል ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በሞሮኮና በደቡብ አፍሪካ እየገነባ ይገኛል᎓᎓

ኩባኒያው ኢትዮጵያ፤ ዛምቢያና ኬንያን ጨምሮ በሌሎች አስር አገራት ውስጥ አገልግሎቱን ለማዳረስ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡

ምንጭ፡ ሮይተርስ