በየቀኑ 7ሺህ አዲስ የሚወለዱ ህጻናት ይሞታሉ:- ተመድ

ጥቅምት 9፤2010

በየቀኑ ሰባት ሺህ አዲስ የሚወለዱ ህጻናት ለሞት እንደሚዳረጉ የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ገለፀ፡፡

የአሁኑ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2000 ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

አምስት አመት ሳይሞላቸው የሚሞቱ ህጻናት በአውሮፓውያኑ 2000 ከነበረው 9.9 ሚሊዮን ሞት በ2016 ወደ 5.6 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱ ተመልክቷል።

መንግስታትና የልማት አጋሮች ከአውሮፓውያኑ 2000 ወዲህ የህጻናትን ሞት ለመከላከል ባደረጉት ጥረት ከአምስት ዓመት በታች ሀምሳ ሚሊዮን ህጻናት ህይወት መታደግ መቻሉን ዩኒሴፍ ገልጿል።

የህጻናትን ሞት ለመታደግ ጠንካራ ስራ ካልተሰራ አሁንም ህጻናት በተወለዱበት ቀን ወይም ከዚያ በኃላ የመሞት እድላቸው ክፍት መሆኑን አስጠንቅቋል።

ምንጭ፡‑ ሲጂቲኤን