ኢትዮጵያ የአምራች ዘርፉ ማእከል የመሆን ተስፋ እንዳላት አንድ ጥናት አመለከተ

ጥቅምት 7፣2010

የአለም ልማት ማእከል በቅርቡ ያደረገው ጥናት ኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ ማእከልነት ከኬንያ ልቃ በመገኘት አዲሲቷ ቻይና እየሆነች ነው ብሏል፡፡

ጥናቱ ከ28 የአፍሪካ ሀገሮች ጋር በማነፃፀር በኬንያ በአምራች ዘርፉ ላይ ለመሰማራትም ሆነ  ለመንቀሳቀስ ውድ መሆኑን አመልክቷል፡፡

በኬንያ ያለው የተማረ የሰው ሀይል እጥረት፣ የሰራተኞች ክፍያ ውድነት፣ የመሰረተ ልማቶችና   የኤሌክትሪክ ሀይል ችግር ሀገሪቷን ተመራጭ እንዳትሆን ካደረጓት ምክንያቶች ዋና ዋናዎቹ መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል፡፡

ጥናቱ በአንጻሩ በኢትዮጵያ ያለው ምቹ ሁኔታ አገሪቷን በአፍሪካ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የአምራች ዘርፉ ማእከልነትን በመያዝ በቀጣይ አዲስቷ ቻይና የመሆን እድል ይኖራታል ብሏል።  

ምንጭ- ዘ ስታር