ኢትዮጵያ የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ማእቀፍ መሪነትን ተረከበች

ጥቅምት 3፣2010

ኢትዮጵያ የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ማእቀፍን ለአንድ አመት እንድትመራ   መሪነቱን ከኡጋንዳ ተረክባለች።

ኢትዮጵያ ለሚቀጥለው አንድ አመት የተፋሰስ ሀገራቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እና  የቴክኒካል አማካሪ ኮሚቴ  ሊቀመንበር ሆና  ታገለግላለች ፡፡

ሐሙስ ጥቅምት 2 ቀን 2010 ዓ.ም በተካሄደው የስልጣን ርክክብ ከኡጋንዳው ሳም ቼፕቶሪስ የሊቀመንበርነቱን ኃላፊነት የተረከቡት የኢትዮጵያ ውሃ፣መስኖና ኤሌክትሪክ ሚንስትር ዶክተር ኢንጂነር ሲለሺ በቀለን የወከሉት ሚንስትር ዴኤታው አቶ ከበደ ገርባ  ናቸው፡፡    

ኢትዮጵያ የመሪነት ድርሻዋን መረከቧ የተገለፀው በኡጋንዳ ኢንቴቤ በተካሄደው 25ኛው የተፋሰስ ሀገራቱ የሚንስትሮች ምክር ቤት የውሃ ጉዳዮች ስብሰባ መጠናቀቂያ ላይ ነው፡፡ 

በስብሰባው ኢትዮጵያን ጨምሮ፣ የቡሩንዲ፣ ኡጋንዳ፣ ሱዳን፣ ኬኒያ፣ ሩዋንዳና ታንዛኒያ ውሃ ሚንስትሮች፣ ባለሥልጣናትና ተወካዮች ተገኝተዋል።

የተፋሰስ ሀገራቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 26ኛው መደበኛ ስብሰባ እ.አ.አ.በ2018 በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

 ምንጭ-ዘ ኢንዲፔንዳንት