ጆርጅ ዊሃ የላይቬሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየመራ ነው

 ጥቅምት 03፣2010

በላይቤሪያ ፕሬዝዳንታዊ የምርጫ የቀድሞ የእግር ኳስ ተጨዋች ጆርጅ ዊሃ እየመራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

የአገሪቱ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን መረጃ መሰረት ጆርጅ ዊሃ ከ15 የምርጫ ጣቢያዎች በ11ዱ ሲመራ አብዛኛው ውጤት እንዳልተቆጠረ ተገልጿል፡፡

ተፎካካሪው የሆነው ም/ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦአኪይ በአንድ የምርጫ ክልል እየመሰራ ሲገኝ ከዊሃ ቀጥሎ ሁለተኛው ሰው ናቸው፡፡ ዕጩ ተወዳዳሪዎቹ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ለመሆን 5ዐ ከመቶ ማሸነፍ እንደሚኖርበት ተገልጿል፡፡ ሁለቱ ተወዳዳሪዎች ይህን ውጤት ማግኘት ካልቻሉ ሁለተኛ ዙር ምርጫ ለሚቀጥለው ወር እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው ምርጫ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ እና የመጀመሪያዋ የአፍሪካ ሴት ፕሬዚዳንት በመሆን ተመርጠው ላይቤሪያን ለ12 ዓመታት የመሩትን ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍን ለመተካት ነው።

ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎችም ባሳለፍነው ማክሰኞ በላይቤሪያ በተካሄደው ምርጫ ይህ ነው የሚባል የጎላ ችግር አልተመለከትንም፤ ምርጫው ስኬታማ ነበር ብለዋል።

በሁለት ዙር ሀገራቸውን ለ12 ዓመታት የመሩት የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት   እንዳሉት ሁሉም ላይቤሪያውያን በዚህ ሂደት ውስጥ መሳተፋቸው አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡