የኢትዮጵያ መንግስትና ፋኦ የገጠር ልማትን በጋራ ለማከናወን ተስማሙ

ጥቅምት 2፤2010

የእርሻና ተፈጥሮ ሃብትና በተመድ የምግብና እርሻ ድርጅት የገጠር ልማትን በተሳካ መልኩ ለማከናወን በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገለጸ፡፡

ሁለቱ ወገኖች የአለም የምግብ ቀንን በማስመልከት በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ  ህይወት እንለውጥ፤ በምግብ ዋስትናና ገጠር ልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ የስደትን አስከፊ ሁኔታን እንቀይር በሚል መርህ ቃል ይከበራን ነው ያሉት፡፡

በኢትዮጵያ የአለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ተወካይ ሃሳን አሊ በበኩላቸው በሀገሪቱ የምግብ ዋስትና እና የገጠር ልማት ስራዎችን ስኬታማ ለማድረግ ድርጅታቸው የደኩሉን እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያን የአግሮ ኢንደስትሪ ለማሳደግ ይረዳ ዘንድ የተባባሪ አካላትን ትብብር ለማጠናከር የምግብ ቀንን መከበር እንደሚጠቀሙበት የእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትር ድኤታ ዳመነ ዳሮታ ተናግረዋል፡፡

 በገጠር አካባቢ የሚገኙ ወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም የአግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮችን ለመገንባት ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የገጠር ልማትን ለማፋጠንና ህገ ወጥ ስደትን ለማስቀረት ሲባል ለ አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ ስራን ለመፍጠር ማቀዱን አብራርተዋልክ፡፡