አዲሱ ሶፍት ዌር የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን የበለጠ ተደራሽ እንደሚያደርግ ተገለጸ

ጥቅምት 2፤2010

አዲስ የተፈበረከው ስፓርክኢድ የተባለ ሶፍት ዌር በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን የበለጠ ተደራሽ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡

 በርሚንግሃም ስፓርክማን ማእከል ለአለም ጤና ስር የሚገኘው የአላባማ ዩኒቨርሲቲ ከዛምቢያና ኢትዮጵያ ሶግትዌር አበልፃጊዎች ጋር በመሆን ነው ይህንን ፕሮጀክት ያከናወኑት፡፡

በአፍሪካ የሚታየውን የመማሪያ መጽሃፍቶች ወይም የትምህርት ቁሳቁሶች አቅርቦት እና የኢንተርኔት እጥረት ችግሮችን ይህንን ሶፍትዌር ለማበልፀግ  እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በአላባማ ዩኒቨርሲቲ  የማህበረሰብ ጤና ትምህርት ቤት ሜዲካል ዳይሬክተር ክሬይግ  ዊልሰን በሁለቱ ሀገሮች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች አማራጭ መፍትሄ  ለማስቀመጥ ቢሞከረም አጥጋቢ እንዳልሆኑ ተናግረዋል፡፡

ሶፍትዌሩ ለሁለቱ ሃገራት የትምህርት  ቁሰቁሶችን ለማጓጓዝ የሚፈጀውን ጊዜና ገንዘብ እንደሚቀንስ ነው የተገለጸው፡፡

በበርሚንግሃም የበለፀገው የኢንተርኔትና የቪዲዮ ኮንፍረንስ መፍትሄ  በኢትዮጵያ የመምህራን እጥረት ባለባቸው አዳዲስ ለሚከፈቱ የህክምና ትምህርት ቤቶት የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን እያቀረበላቸው መሁኑን ሜዲካል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

 ሶፍትዌሩ የተነደፈው ከኢንተርኔት አገልግሎት ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ የኢንተርኔት አገልግሎቱ በሌለባቸው፤ ደካማ ወይም ውድ በሆነባቸው አከባቢዎች በቀላሉ የትኛውንም  የትምህርት  ይዘቶችን በማዘጋጀትና ለማሰራጨት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡ 

ከኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በተደረገው ስምምነት መሰረት ሶፍት ዌሩ ከዘጠነኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ያለውን የመማሪያ መጽሀፍቶችን, ቪዲዮዎችን እና ተጨማሪ ይዘቶችን ጨምሮ ዲጂታል ለማድረግ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

ወደፊትም የተቀሩትን ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍሎች ያሉትን የትምህርት መማሪያ ቁሳቁሶችን ወደ ዲጅታል ፎርማት ለመቀየር እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡

ምንጭ-ኒውስ ዋይዝ