የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዋነኛ ዘርፎች አፈፃፀምና እቅድ እንዴት ይታያሉ?

ጥቅምት 2፤2010

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሰሞኑን ለህዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሠባ የአመቱን የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ አብራርተዋል፡፡

የፕሬዝዳንቱ ንግግር ካተኮረባቸው ዘርፎች መሃከል የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት አንኳር አፈፃፀሞችና እቅድ ይገኝበታል፡፡የኢኮኖሚውን ፈጣን እድገት ለማስቀጠል መንግስት እንደሚወስዳቸው ይፋ ካደረጓቸው እርምጃዎች መካከል የውጭ ንግድን ማሳደግ ይጠቀሳል፡፡ ለዚህ እንዲረዳም የብሄራዊ ባንክ የወለድ ማሻሻያ፣ የብርእና የዶላር ማስተካከያ አድርጓል፡፡

በ2ሺ 8 ኢኮኖሚው የ8 በመቶ እድገት ሲያስመዘግብ በ2ሺ9 1ዐ ነጥብ 9 በመቶ ሆኗል፡፡

ዘንድሮ ደግሞ 11 ነጥብ 1 በመቶ እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው፡፡

በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዋነኛ ዘርፎች አፈፃፀምና እቅድ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡን  የኢፌዴሪ ፕላን ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው አደምን በኢቢሲ እስቱዲዮ በመገኘት በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡