ነዋሪዎች በሰበታ- ምኤሶ -ደወሌ የባቡር መስመርን ሲጠቀሙ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተጠየቀ

ጥቅምት 2፤2010

የሰበታ- ምኤሶ -ደወሌ የባቡር መስመር አገልግሎት መስጠት በሚጀምርበት ወቅት በባቡር መስመሩ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አሳሰበ፡፡

ኮርፖሬሽኑ የባቡር መስመሩ ከሚያልፍባቸው አካባቢዎች ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር በአዳማ ከተማ ተወያይተዋል፡፡