የላይቤሪያ የምርጫ ድምፅ ቆጠራ ተጠናቀቀ

ጥቅምት 1፤2010

የላይቤሪያ የምርጫ ድምፅ ቆጠራ በሰላም መጠናቀቁን የሀገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

የድምፅ ቆጠራው ሲካሄድም የምርጫ ኮሚሽኑ ቢሮ ኃላፊዎችና የፓርቲው ተወካዮች ተገኝተው መታዘባቸው ተገልጿል፡፡

የምርጫ ውጤቱም በፈረንጆቹ ጥቅምት 25 ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ተብሏል፡፡

የላይቤሪያ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ ችግር እንዳላጋጠመ ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንዶች የምርጫ ኮሚሽኑ ስለምርጫው ሂደት ለሕዝቡ በሚገባ አላስተማረም ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

በላይቤሪያ የተካሄደው የአሁኑ ምርጫ ከ14 ዓመት የርስ በርስ ጦርነት በኋላ የተካሄደ ሶስተኛው ምርጫ ነው፡፡

ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው፡፡