የኬንያ ፓርላማ የምርጫ ህግ ማሻሻያ አጸደቀ

ጥቅምት 1፤2010

የኬንያ ፓርላማ  የአገሪቱ የምርጫ ህግ ማሻሻያ አጸደቀ።

በተሻሻለው የምርጫ ህግ መሰረት አንድ እጩ ተወዳዳሪ በድጋሚ በሚደረግ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ራሱን ካገለለ ተፎካካሪው እጩ ተወዳዳሪ አሸናፊ ይሆናል ይላል᎓᎓

የተሻሻለው የምርጫ ህግ ግን ራሳቸውን ከምርጫው ባገለሉ ተቃዋሚዎች ዘንድ ትችት እየቀረበበት ይገኛል᎓᎓

የተሻሻለው የምርጫ ማሻሻያ ህግ ህግ ሁኖ እንዲቀጥል የግድ በፕሬዝዳንቱ ፊርማ መጽደቅ አለበት ነው የተባለው᎓᎓

የኬንያ ተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ የኬንያ ፍርድ ቤት የድጋሚው ምርጫ በአውሮፓውያኑ ጥቅምት 26/2017 ከሚካሄደው ምርጫ ራሳቸውን አግልለዋል᎓᎓

ራሳቸውን ከምርጫው ለማግለል የሰጡት ምክንያት ደግሞ የሚሰጠው ድምጽ ነጻና ፍትሃዊ ስለማይሆን ራሴን ከምርጫ አግልያለሁ ብለዋል᎓᎓

በዚህ ደግሞ ኡሁሩ ኬንያታ ተጠቃሚ ሁነዋል᎓᎓

ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ምርጫው በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይካሄዳል᎓᎓ ባለፈው ነሃሴ ካገኙት ድምጽ በበለጠ ለማግኘት እንደሚሰሩና ፓርቲያቸው ለባዶ ሽንገላና ለከፋፋይ ፖለቲካ ጊዜ እንደሌለው በአጽንኦት መናገራቸውን ሲ. ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል᎓᎓

በሌላ በኩል የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተቀሩት እጩ ተወዳዳሪዎች በድጋሚ ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መወዳደር እንደሚችሉ አስታውቋል᎓᎓

ባለፈው ነሀሴ በተካሄደው የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተወዳድረው ከአንድ ከመቶ በታች ድምጽ ያገኙት እኩሩ አኮት እና ሌሎች 5 ተወዳዳሪ እጩዎች በአውሮፓውያኑ ጥቅምት 26 በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲወዳደሩ የኬንያ ፍርድ ቤት ትእዛዝ አስተላልፏል᎓᎓