አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ጀመሩ

ጥቅምት 1፤2010

አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ በሰሜን ኮሪያ ላይ ጫና ለማሳደር በኮሪያ ልሣነ ምድር ላይ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ መጀመራቸው ተገለፀ፡፡

ቢዋን ቢ ቦምብ ጣይና ሁለት የደቡብ ኮሪያ ኤፍ 15ኬ ሚሳኤል ተሸካሚ ጄቶችም በደቡብ ኮሪያ የውሃ ምድር ላይ የሚሳኤል ሙከራ እያካሄዱ ነው ተብሏል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ወታደሮች እንደገለፁት የቦምብ ጣይ አውሮኘላኖቹ ከዩናይትድ ስቴት የፓስፊክ ግዛት ወደ ደቡብ ኮሪያ ከመግባታቸው በፊት ባህር ላይ የጋር ወታደራዊ ልምምድ አድርገዋል፡፡

የአሜሪካው ኘሬዝዳንት ዶናልድ ትራምኘ ከሰሜን ኮሪያ ሊሰነዘርባቸው ለሚችል ጥቃት  ምላሽ ከመስጠት በከፍተኛ የደህንነት ሃላፊዎች ጋር ከተወያዩ በኋላ ለውሳኔ በመድረሳቸው ነው ተብሏል፡፡

ይህ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሰሜን ኮሪያ ከቅርቡ 6 የኒኩለር ሙከራዎችን ማድረጓን ተከትሎ የተደረገ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡