ምክር ቤቱ ፕ/ት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን አጸደቀ

መስከረም 30፤2010

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው አንደኛ መደበኛ ስብሰባ  ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የ2ዐ1ዐ የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን በማድመጥ አፀደቀ፡፡

ምክር ቤቱ በሶስተኛው አመት የመጀመሪያ መደበኛ ስብሰባው ላይ በኢፌዴሪ  መንግሥትናበዛምቢያ፣በሱዳን፣በኬንያ፣በጅቡቲ፣በጋና፣በኮትዲቫር፣በቼክ ሪፐብሊክ፣ በፊንላንድ፣ በአርጀንቲናና ቬንዙዌላ መንግሥታት መካከል  በቱሪዝም፣ በትራንስፖርትና ሁለንተናዊ በሆኑ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት በተደረጉ ስምምነቶች ላይ ተወያይቶ ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች እንዲሰሩ ውሣኔ አስተላልፏል፡፡

በተጨማሪም የምክር ቤቱን የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

በሣሙኤል ዮሀንስ