አምባሳደር አባዲ ዘሙ ከሱዳን መንግስት ከፍተኛ ሽልማት ተበረከተላቸው

መስከረም 30፤2010

በሱዳን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አባዲ ዘሙ የሀገሪቱን ከፍተኛ ሽልማት ከፕሬዝዳንት ኦማር ሃሳን አልበሽር እንደተበረከተላቸው ተገለጸ፡፡

አምባሳደሩ ከአልባሽር ሽልማቱ የተበረከተላቸው በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማሳደግ እሳቸውና የቢሮ ባልደረባዎቻቸው ላደረጉት ጥረት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

አምባሳደር አባዲ ዘሙ እንደገለጹት ከሆነ ሱዳን በቆዩበት ላለፉት ስድስት አመታት ውስጥ በሁሉም የልማት ዘርፎች በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው ሁለንትናዊ ግንኙነት በከፍተኛ ፍጥነት አድጓል፡፡

በቆይታቸውም ወቅት ለስራቸው ስኬት ድጋፍ ላደረጉላቸው የሱዳን መንግስትና ህዝብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር