የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ተመን ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ወሰነ

መስከረም 30፤2010

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የውጥ ምንዛሪና የወለድ ተመን ፖሊሲ ላይ ማሻሻ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ባንኩ ብር በዶላር ላይ የሚኖረውን የውጭ ምንዛሪ ተመንን በ15 በመቶ ማሻሻያ ማድረጉን የባንኩ ምክትል ገዢ እና ቺፍ ኢኮኖሚስት ዶ/ር ዮሃንስ አያሌው ተናግረዋል፡፡

በማሻሻው መሰረት ብር ዶላርን የሚገዛበት አቅሙ በ15 በመቶ ቀንሷል፡፡ በዚህም መሰረት ዛሬ በባንኮች መካከል ሲደረግ የነበረው የአንድ ዶላር የመግዣ ዋጋ 23 ነጥብ 4177 የነበረው ከነገው እለት ጀምሮ በ26 ነጥብ 9303 ይሆናል ማለት ነው፡፡

በባንኮች የወለድ መጠን ላይ በተደረገው ማሻሻያም አምስት በመቶ የነበረው ዝቅተኛ የወለድ መጠን ወደ ሰባት ከመቶ ከፍ እንዲል ተወስኗል፡፡

ምክትል ገዢው እንዳሉት ከሆነ የውጭ ምንዛሪና የወለድ ተመን ማሻሻው ያስፈለገው ኤክስፖርትን ለማበረታታት እና የሀገሪቱን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ ነው፡፡

በህይወት ደገፉ