አሜሪካ በሱዳን ላይ ጥላው የነበረውን ማዕቀብ እንደምታነሳ ማሳወቋን ማሳወቋን ተከትሎ ኢትዮጵያ ድጋፏን ገለጸች

ጥቅምት 01፣2010

ኢትዮጵያ  አሜሪካ ከ2ዐ ዓመታት በኋላ በሱዳን ላይ ጥላው የነበረውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንደምታነሳ ማሳወቋን ተከትሎ ኢትዮጵያ ድጋፏን ገለጸች፡፡

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳመለከተው ማዕቀቡ ከዚህ በፊት በሀገሪቱ የልማት እድገት ላይ ተፅዕኖ አሳርፎ ቆይቷል፡፡

አሜሪካ ማዕቀቡን ለማንሳት የወሰነችው ሱዳን ግጭት በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ሰላምና መረጋጋትን ለመፍጠር ባደረገችው ጥረት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ሱዳን ለሰብአዊ ድጋፎች ዝግጁ በመሆኗና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት በማሻሻሏ እንደሆነም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ውሣኔው ለሱዳንና ለአፍሪካ ቀንድ ልማት መጎልበት ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ የሱዳን ኢኮኖሚ መሻሻል ለኢትዮጵያና ለቀጠናው ልማት ጠቀሜታው ጉልህ ነው ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ያለው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ጠንካራ የጋራ እሴቶች ያሏቸው ሀገራት በመሆናቸው ውሣኔው ከሁለቱ ሀገራት ባለፈ ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት አስተዋፅኦ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ሱዳን ከቅርብ አመታት ወዲህ ግጭቶችንና አሸባሪነትን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ላደረገችው አበረታች ተግባር ኢትዮጵያ አድናቆቷን ገልፃለች፡፡

በሀገሪቱ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትም የቀጠናው የጋራ ትብብር እንዲጎለብት ኢትዮጵያ እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡