አንድ የቻይና ግዙፍ ኩባንያ የአፍሪካ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪን ተቀላቀለ

መስከረም 25፣2010

አንድ የቻይና ግዙፍ የኮንስትራክሽን ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ሀገራት ያለውን ቢዝነስ በተሳካ መልኩ ማስፋፋቱን ገለፀ፡፡

‹‹ሊቦ›› በሚል የሚጠራው ይህ ኩባንያ ቻይና እ.ኤ.አ በ2013 ይፋ ያደረገችው በ‹‹ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሼቲቭ›› የትብብር ማዕቀፍ የፈጠረውን ምቹ እድልን ተከትሎ ነው በአፍሪካ ቢዝነሱን ያስፋፋው፡፡

‹‹ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሼቲቭ›› ቻይና ከአፍሪካ፣ ኢሲያና አውሮፓ ሀገራት ጋር በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ በመሰረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር የፈጠረችው የትብብር ውጥን ነው፡፡

በዚህም መሰረት እ.ኤ.አ በ2006 የተቋቋመው ኩባንያው ይህንን ምቹ እድል በመጠቀም በተለይ በኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ሀይል ዘርፍ ተሰማርቶ እንደነበር ተነግሯል፡፡

ባለፈው ዓመት ከበርካታ የሀገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር በመተባበርም 237 ኪሎ ሜትር እርዝመት ያለው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ገንብቷል ተብሏል፡፡

107 ሚሊዮን ዩዋን የተመዘገበ ካፒታል ያለው ኩብንያው በስሩ 500 ሰራተኞን ቀጥሮ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ኩባንያው ‹‹ቲቤት›› ከተባለ የቻይና ራስ ገዝ ክልል የወጣ ሲሆን ሌሎች ከ10 የሚልቁ ኩብንያዎችም በትብብር ማዕቀፉ የተፈጠረውን እድል በመጠቀም ቢዝነሳቸውን ወደ ሌሎች የአለም ሀገራት እንዳሸጋገሩም ተጠቁሟል፡፡ 

ምንጭ፦ ሽንዋ