ፌስ ቡክ ህንዳውያን ደም የሚያገኙበትን መንገድ ለማገዝ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

መስከረም 19፣2010

ፌስ ቡክ ፈስቡክ ከአውሮፓያኑ ጥቅምት  1/2017  በህንድ ብዛት ካላቸው ደም ለጋሾች ለሆስፒታሎች፣ ለደም ባንክና ደም ለሚያስፈልጋቸው ግለሰቦች የሚሆን ደም ለማሰባሰብ የሚያግዝ አዲስ ዘዴ ተግባራዊ ሊያደርግ ነው።

ህንዶች በፌስ ቡክ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይገናኛሉ ፎቶዎችን ይለዋወጣሉ የደምን ልገሳንም ይፈልጋሉ ተብሏል᎓᎓

በህንድ የደም እጥረት አለ። መጠኑ ከተማ ከተማ መጠኑ ቢለያይም  አገሪቷ የምታገኘው ደም ከሚያስፈልጋት መጠን 10 ከመቶ ያነሰ ነው ተብሏል᎓᎓

በመሆኑም ህሙማንና ቤተሰቦቻቸው ህሙማኑ የተጠቀሙትን ደም መልሰው ወደ ደም ባንከ የማስገባት ሃላፊነት እንዳለባቸው ነው የተገለጸው᎓᎓

የተበደሩትን ደም ወደ ደም ባንከ ለመመለስ ብዛት ያላቸው ሰዎች ወደ ማህበራዊ ሚዲያና ወደ ፌስ ቡከ በመግባት የደም ለግሱን ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ᎓᎓

አዲሱ የፌስ ቡክ ዘዴ የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች በአንድሮይድ ስልክ  ወደ ድረ ገጽ በመግባት ህጋዊ ደም ለጋሽ ለመሆን ይመዘገባሉ᎓᎓

የደም አይነታቸውን ከዚህ በፊት ደም ለግሰው ያውቁ እንደሆነ ይጠየቃሉ᎓᎓ ይህ መረጃ ለሁም ሰው ይደርሰዋል᎓᎓ መረጃው የደረሰውም ሀሳቡን በመጋራት ሌላ ሰው እንዲያየውና በጉዳዩ ላይ ግንዛቤ  እንዲኖረው ያደርጋል መባሉን የዘገበው ሲ ኤን ኤን ነው᎓᎓