በሺዎች የሚቆጠሩ የሀሰት አካውንቶች መዝጋቱን ፌስ ቡክ ገለጸ

መስከረም 18፣2010

በጀርመን አጠቃላይ ምርጫ ወቅት ሲሰራጩ የነበሩ የሀሰት ዜናዎችንና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የሀሰት አካውንቶችን ሲዘጋ እንደነበር ፈስ ቡክ አስታውቋል።

የአውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅና የአፍሪካ የፌስ ቡክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪቻርድ አላን የሀሰት ፕሮፈይሎችን የመዝጋት ሂደቱ በምርጫው ወቅት የተላለፉ የተዛቡ መረጃዎችን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ባያስችልም የስርጭታቸውን አድማስ ግን መቀነስ ተችሏል ብለዋል᎓᎓

ፕሬዝዳንቱ የማህበራዊ ሚዲያ ኔትዎርክ የሰዎችን የተዛባ አመለካከት ማንጸባረቂያ እንዳይሆን መቆጣጠር አለብንም ብለዋል᎓᎓

የፌስ ቡክ ኩባንያ እርምጃውን ለመውሰድ የተገደደው በፈረንሳይና በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወቅት የውጪ ጣልቃ ገብነት ነበር የሚለውን ሪፖርት በተደጋጋሚ በመስማቱ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።