በሊቢያ የባህር ዳርቻ ካለነዳጅ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ተገልብጣ የ8 ስደተኞች ህይወት አለፈ

መስከረም 12፣2010

በሊቢያ የባህር ዳርቻ ካለነዳጅ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ተገልብጣ የስምንት ስደተኞች ህይወት አለፈ፡፡

5ዐ የሚሆኑት ደግሞ ሳይሰምጡ እንዳልቀረ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የአከባቢው ባለስልጣናት እንዳሉት ጀልባዋ 1መቶ ያህል  ስደተኞችን አሳፍራ ባለፈው ሳምንት አርብ ነበረ ከሊቢያዋ የምዕራብ ከተማ ሰባርታ የተነሳችው፡፡

ጀልባዋ ከመገልበጧ አስቀድሞ ለቀናት ተንሳፋ መቆየቷንም የአይን እማኞች ገልፀዋል፡፡

35 ስደተኞች በህይወት የተገኙ ሲሆን ሁሉም ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት የሄዱ ናቸው ተብሏል፡፡

ሊቢያ በባህር ወደ ደቡብ አውሮፓ ለመድረስ የስተደኞች ዋነኛ መሸጋገሪያ መስመር ናት ፡፡

ባለፈው አመት ብቻ 1ዐዐሺ ያህል ስደተኞች የሜድትራኒያን ባህርን አቋርጠው ወደ ጣሊያን ገብተዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ሪፖርትን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው በተመሳሳይ ዓመት ከ2ሺ 4ዐዐ በላይ የሚሆኑት ስደተኞች ህይወታቸውን  አጥተዋል፡፡