የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከሱዳኑ አቻቸው ጋር ተወያዩ

መስከረም 11፣2010

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከሱዳኑ አቻቸው ፕሮፌሰር ኢብራሂም ጋንዱር ጋር በኒውዮርክ ተገናኝተው በሁለትዮሽ እና አካባቢያዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ዶክተር ወርቅነህ እንዳሉት በተለያዩ ጉዳዮች ተይዘው በሱዳን ማረሚያ ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲለቀቁና ወደ አገራቸው የሚመለሱበት ቀን እንዲፋጠን ጠይቀዋል፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ጋንዱርም ለጥያቄው ይሁንታቸውን መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡