የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የቴክኖሎጄ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል :-ጠ/ሚ ኃይለማርያም

መስከረም 11፣2010

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ  የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የቴክኖሎጄ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገለፁ፡፡

ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ አገሮች መድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑት ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዳሉት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ቅድሚያ የሚሰጡትን የልማት መርሃ ግብራቸውን ውጤታማ እንዳያደርጉ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥረውን የአየር ንብረት ለውጥ እንዲቋቋሙ የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ መሆኗን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በቅርቡ የደረሰው ድርቅ ለችግሩ ተጋላጭነቷን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የበለፀጉ አገራት በአየር ንብረት ለውጥ ለተጋላጭ ለሆኑ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ በገቡት ቃል መሰረት ተግባራዊ አለመድረጋቸውን አንስተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ታዳጊ አገሮች ለአረንጓዴ ልማት ውጤታማ የሆኑ ኘሮጀክቶችን መቀየስ እንዳለባቸውና ለዚህም የአቅም ግንባታ ተግባራት እንደሚያስፈልጋቸው መግለፃቸውን ሪፖርተራችን እናትአለም መለሰ ዘግባለች፡፡