ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ከሆኑ አምስት የአፍሪካ አገራት አንዷ ናት-ራንድ መርቻንት ባንክ

መስከረም 09፣2010

ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ 2018 ከፍተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከሚኖራቸው አምስት የአፍሪካ አገሮች አንዷ መሆኗን ራንድ መርቻንት ባንክ ያወጣው ሪፖርት አመለከተ።

ባንኩ በ2018 ትንበያው እንዳመለከተው ግብጽ ደቡብ አፍሪካን በማስከተል ከአህጉሩ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆናለች። ኢትዮጵያ ደግሞ ሞሮኮን ተከትላ አራተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻነትን ይዛለች።

የአፍሪካ ኮርፖሬትና ኢንቨስትመንት ባንክ የሆነው ናት-ራንድ መርቻንት ባንክ ጋና አምስተኛ ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬንያ ደግሞ በስድስተኛ ደረጃ አስቀምጧታል።

በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እየገሰገሰች ያለችው ኢትዮጵያ የአሜሪካና የቻይና ባለሀብቶችን ጨምሮ በርካቶች የሚመርጧት የምስራቅ አፍሪካ ትልቋ የኢኮኖሚ ባለቤት መሆኗን ሪፖርቱ አመልክቷል።

ምንጭ፤ራንድ መርቻንት ባንክ