የሱዳን ፕሬዝዳንት ለጄኔራል ሳሞራ የኑስ የሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን አበረከቱ

መስከረም 08፣2010

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ ሚና እንዲጫወት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ከሱዳን ፕሬዝዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር የሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን ተበረከተላቸው፡፡

ሽልማቱ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በሀገር ውስጥ እንዲሁም በቀጠናው ላበረከተው አስተዋፅኦ የተሰጠ መሆኑን የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ገልፀዋል፡፡