ጠ/ሚንስትሩ ለአቶ ዛዲግ አብርሃ በሚንስትር ማዕረግ ሹመት ሰጡ

መስከረም 08፣2010

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ቀድሞ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩትን አቶ ዛዲግ አብርሃን የሚንስትር ማዕረግ ሹመት ሰጡ፡፡

አቶ ዛዲግ ከመስከረም 1 ቀን 2ዐ1ዐ ዓመተ ምህረት ጀምሮ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት ዴሊቨሪ ዩኒት ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡