ከሚሊኒየሙ መባቻ ወዲህ ያሉ ዋና ዋና ስኬትና ተግዳሮቶች

ጳጉሜ 4፣2009

በኢትዮጵያ ባለፉት 1ዐ አመታት ለተከናወኑት ተግባራት ለ1ዐ ሚሊዮን ሰዎች የስራ መፍጠር መቻሉን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በሚሊኒየሙ መባቻ በኢትዮጵያ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን የሞባይል ተጠቃሚዎች ነበሩ፡፡ አኃዙ ከ1ዐ አመታት በኋላ ወደ 58 ነጥብ 1 ሚሊዮን አድጓል፡፡

የከፍተኛ የመንግስት ተቋማት ከ22 ወደ 43 አድገዋል፡፡

በሀገሪቱ የነበረው የጤና ሽፋንም ከ89 ነጥብ 6 በመቶ ወደ 98 ነጥብ በመቶ ከፍ ብሏል፡፡

የዜጎች ዕድሜ ጣሪያ ከ44 አመት ወደ 65 አመት ማደጉ

በሃይል ልማትም ሀገሪቱ ከነበራት 2 ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ወደ 4 ሺህ 269 ሜጋ ዋት አድጓል፡፡

ሆኖም በሀገሪቱ የተጠበቀውን ያህል ለውጥ ያላሳዩ ዘርፎችም አሉ፡፡

ኢንዱስቱሪው በሚፈለገው መጠን አለማደጉ፣ ግብርናው አለመዘመኑ፣ የትምህርት ጥራት በሚፈለገው መጠን አለማደግ፣ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ የመሳሰሉ ችግሮች እስካሁን ያልተሻገርናቸው መሆናቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

በእዮብ ሞገስ