የማህበራዊ ሚዲያ ጎብኚዎች የመረጃዎችን ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለባቸው፦ተመድ

ጳጉሜ 3፣2009

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መረጃዎችን ሲቀበሉና ሲያስተላልፉ ትክክለኛነታቸውን በማረጋገጥ መሆን እንዳለበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት ፎረም በውሸት ዜናዎች ዙሪያ ያተኮረ ውይይት አካሄዷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመለየት ውስብስብ እየሆነ መምጣቱን በውይይቱ ተመልክቷል፡፡

ሆኖም የማህበራዊ ሚዲያ ጎብኚዎች እውነተኛ ባልሆነ መረጃ እንዳይታለሉ ብሎም እንዳያሰራጩ መረጃው ትክክል መሆኑን ከታማኝ ምንጮች በማመሳከር መጠቀም እንዳለባቸው ተነግሯል፡፡

በህገወጥ መንገድ የታዋቂ የሚዲያ ተቋማትን ስም በመጠቀም የውሸት መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ተጠያቂ እንዲሆኑ እና ጋዜጠኞች ከተለያዮ አደጋዎች የተሻለ ከለላ እንዲያገኙም ተጠይቋል፡፡

ሚዲያዎች የጋዜጠኝነትን መርሆዎች በመከተል የህዝብ ድምጽ በመሆን የሚታመኑ እንዲሆኑ መስራት እንዳለባቸው ተጠቅሷል፡፡

ጋዜጠኞችም ለተደራሲያን ስለየውሸት ዜናዎች መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ ግንዛቤ መፍጠር ይገባቸዋል ተብሏል፡፡

በውይይቱም በየጊዜው እየጨመሩ የመጡትን የውሸት ዘገባዎችን ስርጭት ለመከላከል በሚያስችሉ መፍትሄዎች ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

ምንጭ፦ ተመድ