ትምህርት ሰላማዊ ሃሳቦች እንዲንሸራሸሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው:- ተመድ

ጳጉሜ 3፣2009

ትምህርት ሰላማዊ ሃሳቦች እንዲንሸራሸሩ እኩልነትና መከባበር እንዲዳብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ᎓᎓

የድርጅቱ ሃላፊዎች ይህን ያሉት የሰላም ባህል እንዴት ማዳበር እንችላለን አሁን አለማችንን ያጋጠሟት አለመረጋጋቶች ለመፍታት የሰላም ባህልን ማዳበር በሚቻልበት ሁኔታ በመከሩበት ነው።

የጠቅላላው ጉባኤ ፕሬዝዳንት ፔተር ቶምሰን በኒውዮርክ በልጆች እድገት ላይ የሚያተኩረውን ስብሰባ ሲከፍቱ እንደተናገሩት "ልጆቻችንን ስለ ሰላም፣ መቻቻል እኩልነትና መከባበር እሴቶች  ማስተማር አለብን ብለዋል᎓᎓

ራሳቸውን የሚጠሉበትን ሁኔታ ማስወገድ ይገባልም ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ልጆቻችንን በክህሎትና በትምህርት በማበልጸግ ግጭቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ ፍትሃዊ ያልሆኑ ነገሮችና አለመቻቻል ሲያጋጥም መቃወም እንዳለባቸው ሁሉንም አይነት መድልዎና ጥላቻን እንዲያስወግዱ ማስተማር ይገባናል ብለዋል።

ሰላማዊና ፍትሃዊ የሆነ ማህበረሰብ መገንባት ድህነትን ለመቀነስ፣ ሁሉን አቀፍ ብልጽግና ለማምጣት፣ የሰብአዊ መብትን ለማስከበር፣ ህግን ለማክበር ውጤታማና ተጠያቂ ተቋማትን ለመገንባት ቀጣይነት ያለው እድገት የማምጣት አጀንዳን ለመተግበር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ገልጸዋል።

ምንጭ:-የመንግስታቱ ድርጅት ድረገጽ