የአፍሪካ ግብርና 1 ትሪሊዮን ዶላር የሚሆን የምግብ ገበያ የመሸፈን አቅም አለው:-ሪፖርት

ጳጉሜ 2፣2009

በአፍሪካ በትናንሽ ማሳዎች የሚያርሱ አርሶ አደሮችና የግብርናው ንግድ መስክ   በአውሮፓውያኑ 2030 በየአመቱ የአንድ ትርሊዮን ዶላር የሚያወጣ የምግብ ገበያ ሊሽፍኑ እንደሚችል አንድ ሪፖርት አመለከተ።

የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት የ2016 የአህጉሪቱን የግብርና ሪፖርት ይፋ ደረገበት ጥናቱ የስራ ፈጠራ እና ነጻ ገበያ እያደገ ያለውን የአፍሪካ ምጣኔ ሀብታዊ እድገት የምግብ ገበያውን እያሳደገው ይገኛል። ይህም በአህጉሪቱ ያለው የምግብ ፍላጎት ለማሳደግ ምቹ አጋጣሚ መሆኑ ሪፖርቱ አመልክቷል።

በአውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር በ2030 በከፍተኛ ዋጋ ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በአፍሪካ ምርቶች በመተካት በየአመቱ ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ያስገኛል ብሏል ጥናቱ።ይህም በማዕደን ዘርፍ ከሚገኝ ገቢ ይሸፈናል ተብሎ ሲሰራበት የቆየውን ያልተሳካ አካሄድ እውን ማድረጊያ መንገድ ይሆናል ብሏል ሪፖርቱ፡፡

ሪፖርቱ እንዳመለከተው የአፍሪካ እርሻ በአነስተኛ ማሳ አርሶ አደሮች ምርታማነትን በሚጨምሩ ስራዎች  የተረጋጋ የኢኮኖሚ እድገት መፍጠር ላይ ያተኮረ ነው።

በአሁኑ ወቅት 37 በመቶ የሚሆነው የአህጉሪቱ ህዝብ የሚኖረው በከተሞች አባቢ መሆኑን ያመለከተው ሪፖርቱ፣ አብዛኛው ስራም አነስተኛ ክፍያ፣ ዝቅተኛ ምርት ባለው አገልግሎት የሚሰሩ መሆናቸውን አመልክቷል።

የአህጉሪቱን አጠቃይ ዓመታዊ ምርት የሚሸፍነው ይኸው ዘርፍ በአግባቡ ታቀዶ ከሰተሰራበት ፈጣን የዘርፉን ለውጥ ማረጋገጥ እንደሚያስችል ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡  በአህጉሪቱ በምግብ ምርቶች የሚደረጉ  የምግብ ኢንቨስትመንቶች የአፍሪካን የምግብ ሁኔታ በከፍተኛው ሁኔታ ሊቀይሩት እንደሚችሉ አትቷል።

የአፍሪካ የአረንጋዴ  ልማት ጥምረት ፕሬዝዳንት ዶክተር ኤግኔስ ካሊባታ አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ሀብት፣ እያፈራች ባለችው የሰለጠነ የሰው ሀይል እና በቂ መሬት  አፍሪካ  በተዘጋጁ ምግቦች ብቻ ከገዥነት ወደ ላኪነት ትሸጋገራለች ብለዋል።

ሪፖርቱም እርሻ በግብርና ምርቶች ሁሉን አቀፍ ለውጥ በማምጣት አህጉሪቱን ወደ ብልጽግና እንደሚያሸጋግረው ያሳያል ብለዋል።

አፍሪካ ቀሪው አለም ሰፋፊ እርሻዎችን በመጠቀም በምግብ ኢዱስትሪው ላይ ካመጣው ለውጥ በተቃራኒ የአፍሪካዊያን አነስተኛና መካከለኛ አርሶ አደሮችን በግብርና ማቀነባበር ቴክኖሎጂ ከታገዙ ስኬታማ የሚኮንበት አዋጩ መንገድ መሆኑንም ሪፖርቱ አስቀምጧል፡፡

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ አሁን ላይ አፍሪካ በየዓመቱ ከውጭ ለምታስገባው የምግብ ፍጆታ 35 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ታደርጋች፡፡ይህ ማለት የአነስተኛ አርሶአደሮችን ምርትና ምርታመነትን በዘመናዊ የግብርና አሰራር ማገዝ ከተቻለ አያደገ የሚመጣውን የአህጉሪቱን ፍላጎት ከመሸፈን ባለፈ በአለም ገበያ ውስጥ መግባት ያስችላል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡‑አፍሪካ ቢነስ