የኢጋድ አጋሮች ከጣሊያን ወታደሮች ጋር በመተባበር አክራሪነትን ለመከላከል እንደሚሰሩ ገለጹ

ጳጉሜ 1፤2009

የኢጋድ አጋሮች ከጣሊያን ወታደሮች ጋር በመተባበር አክራሪነትን ለመከላከል እንደሚሰሩ ገለጹ።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አክራሪነትን የመከላከልና የመቆጣጠር የልህቀት ማእከል አክራሪነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር  የህግ አስፈፃሚ አካላት የህግ ማእቀፎችን ተግባራዊ ሊያደርጉ የሚችሉበትና የህብረተሰቡ ተሳትፎ በሚመለከት የሶስት ቀናት አውደ ጥናት በጂቡቲ  አካሄዷል፡፡

በአውደ ጥናቱ ላይ 40 የሚሆኑ ህግ አስፈፃሚ አካላት፣ ሲቪል ማህበራት እና የኢጋድ አባል ሀገራት የማህበረሰብ መሪዎች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡

የአውደ ጥናቱ ዋና አላማ አክራሪነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር  በህብረተሰቡና በህግ አስፈፃሚ አካሉ መካከል ያለው አጋርነት የማበረታታት እና የማጠናከር ስትራቴጂዎች ላይ የተኮረ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ- ኢጋድ